የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር አተረፈ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር አተረፈ!
*****************************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2023/24 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን እያበሰርን፤ ለውጤቱ መመዝገብ ከፍተኛውን ድርሻ ላበረከታችሁ የተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሠራተኞቻችን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን። በበጀት ዓመቱ ብር 135.4 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ13% ዕድገት አሳይቷል። በዚህ ዓመት ከታክስ በፊት የተገኘው ብር 25.6 ቢሊዮን ትርፍም በባንካችን ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል። ለተገኘው ትርፍ ባንካችን የተገበራቸው የወጪ ቅነሳ ስትራቴጂ እና የለውጥ ሥራዎች አስተዋጽዖ አበርክተዋል። የባንካችን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከብር 1.17 ትሪሊዮን የተሻገረ ሲሆን የደንበኞቻችን ቁጥር ደግሞ ከ45 ሚሊዮን በላይ ሆኗል። ባንካችን በበጀት ዓመቱ ከብር 218 ቢሊዮን በላይ የብድር አገልግሎት ያቀረበ ሲሆን፤ 91% ወይም ብር 198 ቢሊዮን የሚበልጠው ለግሉ ሴክተር የተለቀቀ ብድር ነው። የባንካችን አጠቃላይ የተበላሹ ብድሮች ክምችት ከፍተኛ መሻሻል በማሳየት በዓመቱ ማጠቃለያ 2.6% ደርሷል።

የባንካችንን የአምስት ዓመት መሪ እቅድ መሰረት አድርጎ እየተተገበረ የሚገኘው የሪፎርም ስራ ፍሬያማ በመሆኑ የተበላሹ ብድሮች ክምችት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ ባንካችን ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ተቋም እንዲሆን፤ እንዲሁም የወጪ ቁጠባ እንቅስቃሴያችን ውጤታማ እንዲሆን አስችሏል። በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ በቁጥር ከ1.56 ቢሊዮን የሚበልጥ ግብይት፤ ወይም በገንዘብ ከብር 31.6 ትሪሊዮን በላይ የገንዘብ ዝውውር ሲፈፀም፤ ከዚህ ውስጥ በቁጥር ከ1.19 ቢሊዮን ወይም 72% የሚሆነው ግብይት በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የተከናወነ ነው። ይህ ከፍተኛ የሆነ እድገት ላይ የተደረሰው ባንካችን ለዲጂታል ክፍያ ስርዓቶች ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ፣ አገልግሎቶቹን ለደንበኞቻችን ምቹ እንዲሆኑ በማስቻል፣ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን በአጭር ጊዜ በማስፋፋታችን ነው። ይህም ለደንበኞቻችን አገልግሎትና ተያያዥ ሥራዎች መቀላጠፍ ጉልህ አስተዋፅኦ በማበርከት ወጪን ለመቀነስ አስችሏል።
ባንካችን የማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣትና ሁሉንም የማህበረሰብ አካል ተጠቃሚ ለማድረግ በሚሰራው እንቅስቃሴ ሁሉ በመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚሰሩ ልማታዊ እና ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፎችን በስፋት አካሂዷል። ለዚህም መጠነ ሰፊ በጀት በመመደብ በባንካችን ስም የተሰየመውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእግር ኳስ ቡድን ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማብቃታችን ለሊጉ ትልቅ ድምቀትን ፈጠሯል። ከዚህም ባሻገር የ“ፅዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄን በመሪነት በመደገፍ ባንካችን ብር 23 ሚሊዮን አበርክቷል።
በሌላ በኩል ባጠናቀቅነው በጀት ዓመት ባንካችን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች የገጠሙት ቢሆንም፣ እነዚህን ተግዳሮቶች በመቋቋም ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻላችን የባንካችንን ጥንካሬ ብሎም አይበገሬነት ማሳያ ነው።
ከሲስተም ማሻሻያ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለ አግባብ ተወስዶ ከነበረው ብር 801.4 ሚሊዮን ገንዘብ ውስጥ 99.34% ወይም ብር 796.6 ሚሊዮን የሚሆነውን ማስመለስ የተቻለ ሲሆን ቀሪውን ብር 4.76 ሚሊዮን ለማስመለስ ጥረቶች ቀጥለዋል።
በተገኘው አመርቂ ውጤት በመበረታታት በአዲሱ በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በበለጠ ተነሳሽነትና ትጋት መስራት ይጠበቅብናል። የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ሥራ አመራር አባላት የሚሰጡትን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እና የላቀ አገልግሎት በማቅረብ የደንበኞቻችንን እርካታ ከፍ ለማድረግ መትጋት ይኖርብናል።
በመጨረሻም ደንበኞቻችን አብራችሁን በመሆን ለውጤቱ መሳካት ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ በድጋሚ እያመሰገንን፣ በአዲሱ በጀት ዓመትም ከባንካችን ጎን በመቆም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በምናደርገው ጥረት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ እንተማመናለን።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!”

2 thoughts on “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር አተረፈ!”

  1. 1plusgame: Top Slot Online in the Philippines. Easy Login, Register, and Download App via Official Link. Experience 1plusgame, the top slot online in the Philippines. Use our official link for fast 1plusgame login, easy register, and 1plusgame download app. Join and win now! visit: 1plusgame

  2. [7329]Panaloko Online Casino: Best Philippines slots and gaming. Easy Panaloko login, register, and official app download for an elite experience. Join Panaloko Online Casino, the Philippines’ top destination for elite slots. Easy Panaloko login, quick Panaloko register, and official Panaloko app download for a premium gaming experience. Play the best Panaloko online casino games today! visit: panaloko

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Social Media Auto Publish Powered By : XYZScripts.com
Scroll to Top